BORDERING, FINALITY AND BEING BINDING


They say honesty is actually a blunt instrument which bloodies more than it cuts. I don’t know if that is true in the “walking-around-folks” life.  In a politically constrained lawyerly game however even such callous and calculative utterance tantamount to an understatement. Judge this for yourself by looking at the behavior of the Ethiopian and Eritrean government on the boarder dispute. It is the Eritrean government which apparently trying to paint legality and honesty on itself   with regard to the disposition of the boarder claim. The hypocrisy is aggravated exponentially when one comes to see that the crude truth of the dispute is not the boarder line per se in the first place.

እንደዉ ምን ይሻላል?


1-   እጅግ ዉብ የሆነዉ የቅድመ ሴት አያቶቻችን አእምሮ ካቲከላ እንዴት እንደሚወጣ ከተፈላሰፈበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባለዉ ረጅም ዘመን  ኢትዮጵያ ዉስጥ የተፈጠረ ሌላ  አዲስ  ነገር ቢኖር ቲም ለማ የሚባል የፖለቲካ ኃይልና  አብይ አህመድ የሚባል ሰዉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ሆኖ ስልጣን መያዙ ነዉ፡፡ በዚህ ረገድ ራስ ተፈሪና ከኮሎኔል መንግስቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ጋር  የሚያመሳስላቸዉ ነገር ካለ  ወደኃላ እመለስበታለሁ፡፡
2-  ያም ሆኖ  ብዙ ሰዎች  በል ቀልድህን አቁም እንደሚሉኝ አዉቃለሁ፡፡ ቢያንስ የ1967 ዓ.ም መሬትን ከግለሰቦች ቀምቶ  የመንግስትና የሕዝብ ያደረገዉን  አዋጅን፤ በዛዉ ዘመን የታወጀዉን የሙስሊም በዓላትን የሕዝብ በዓላት ያደረገዉን የእኩልነት አዋጅን እና የኢህአዴግ ሠራዊት ደረግን የጣለበትን ተዓምር ከምን ጣልካቸዉ የሚሉ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ የሶማልያ ወረራ ጊዜ  በስድስት ወር ስልጠና ደርሶ በሩጫ  ያባረረዉን የሚሊሺያ ጦር ጀግንነተስ የት አደረስከዉ የሚሉም ይኖራሉ፡፡ ጥያቄዎቹ ሌላ ጥያቄን የሚፈጥሩ ይመስሉኛል፡፡ መሬትን በደምሳሳዉ ከዜጎች መዉረስ ይገባል አይገባም የሚለዉን ነጥብ እንኳን ወደ ጎን ብንተወዉ፤ አሁን ከአርባ አራት ዓመት በኃላ መሬት የሕዝብ ቀርቶ የመንግስት ስለመሆኑ በበቂ ማስረዳት የሚችል ሰዉ ወዲህ ና ሊለኝ ይገባል፡፡ ይህ ሰዉ፤ ጊዜ ያነሳዉ ካድሬ በርግጥ የመሬት ባለቤት አለመሆኑን የማሳየት ከባድ ሽክም በትከሻዉ ተሸክሟል፡፡ የሙስሊም በዓላትን የሕዝብ ያደረገዉ ዓዋጅ  ትልቅ የእኩልነት ዓዋጅ ነዉ፡፡ ነገር ግን እኩልነት በዓዋጅ ይገለጻል እንጂ አይከበርም፡፡ እኩልነት የሚከበረዉ በተግባር ነዉ፡፡ የኢህአዴግ ሠራዊት በደረግ ላይ የተቀዳጀዉ ድልም አርዓያ ስራ ነዉ፡፡  ሆኖም ወተት ይሽፍታል እንኳን ሰዉ ሲገፋ ስለሆነ የአገራችን ታሪክ፤ አንዱ ኃይለኛ በሌላ ባለተራ ከወንበር ሲፈነገል ነዉ የዘመን ዕድሜያችንን ሁሉ ያባጀነዉ፡፡ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ይልቁንስ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት መቶ-በመቶ በምርጫ አሸንፌለሁ የሚል የፖለቲካ ኃይል ምንም የተለየ ለዉጥ በሌለበት ሁኔታ፤  ተመረጥኩ ባለ ስድስት ወርም ሣይሞላዉ በተቃዉሞ ሲርድ ማየት አዲስ ነገር ነዉ፡፡  ማሰብ ለሚችል ሰዉ ክስተቱ አንድ ነገር ብቻ  የሚያሳብቅም ይመስለኛል፡፡ መራጩ  ሕዝብ ከዉጭ አገር የመጣ መሆን አለበት፡፡ የሶማሊያን ወረራ በአጭር ጊዜ መክቶ ያባረረዉ የሚሊሺያ ጦር ታሪክ አዲስ ነገር ነዉ የሚል ሰዉ፤ የራሱን ስንቅና መሣሪያ ይዞ  ስንት ወር በእግር ተጉዞ ጣሊያንን አድዋ ላይ  ድል ያደረገዉን ጀግና ታሪክ ለማድበሰበስ የሚናገረዉ ነዉ ብዬ ለመጻፍ አስብኩና ሰዉ ሊቀየመ ይችላል ብዬ ትቼዋለሁ፡፡
3-  ወደ ነጥቤ ልመለስ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ  አሕመድ  ርዕሰ-መስተዳድር  መሆንን አዲስ የሚያደርገዉ፤ በሕዝብ ሳይመረጡ በአብላጫዉ ሕዝብ ተወዳጅ መሆናቸዉ አይደለም፡፡ የተወዳጅነታቸዉ ምክንያትና  ስፋት ከዓብይ አሕመድ ጋር የሚለያይ ቢሆንም በአጭሩ የታሪካችን ዘመን ሁለት ተመሳሳይ ምሣሌዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ራስ ተፊሪ መሓል ሰፋሪን ይዘዉ በአልጋወራሽነት  ዘመናቸዉ  በጥልቁ  ተወዳጅ ነበሩ፡፡ አለበለዚማ  የወቅቱ  ጎምቱ  ባለኃይሎች  ቁጭ ብለዉ የሰቀሉትን ሲፈልጉ  ቁመዉ ማዉረድ አይሳናቸዉም ነበር፡፡ መንግስቱ ኃይለማርያም  በአብዮቱ የመጀመሪያ ወቅት ተወዳጅነት አልነበራቸዉም ማለት አይቻልም፡፡ ቢያንስ ለዕድገት በኅብረት ዘመቻ  በጃንሜዳ  የከተመዉ ዘማች  የ "መንጌ-መንጌ"  ጆሮ አደንቁር ጭኾት እንደ ናሙና ከተወሰደ፤ የጀርመን ሕዝብ ለሒትለር የጣሊያኑ ለሙሶሎኒ  ከመነሻዉ የሰጠዉን ልብ የሚያማልል ድጋፍ  የሚገዳደር ነዉ፡፡ በመጨረሻ  ግን  የራስ ተፈሪም ሆነ የኮሎኔል መንግስቱ የዕጣ-ፈንታ በአብዛኛዉ በግለሰቦቹ አለቅጥ የተለጠጠ የሥልጣን ጥም ምክንያት የሆነዉን ሆኖ መጠናቀቁን  የምናዉቀዉ ነዉ፡፡ ታዲያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ መጀመሪያቸዉስ  የአማረ ነዉ  መጨረሻቸዉን  የሚያመር እንዲሆን ምን ማድረግ ይገባቸዉ   ይሆን፡፡  
4-  አሁን ባለንብት ሁኔታ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አኪሊስ ሂል የእሳቸዉ የአልተገደበ የሥልጣን ጥም ሳይሆን  ሕጋዊ  ስልጣናቸዉን በአግባቡ እንዳይጠቀሙ የተጋረጠባቸዉ እክል ነዉ፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች ተጠቃለዉ  ከሁለት አቅጣጫዎች ሲመጡ ይታዩኛል፡፡
5-  የመጀመሪያዉ የዓዋጁን በጆሮ ዓይነት ነዉ፡፡ ጠቅላይ ሚነስትር ዓብይ አሕመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ይሁኑ  እንጂ ሩሓቸዉ  ከኒዎ ሊብራል ፍልስፍና  ነዉ ከሚሉት ወገን ይመነጫል፡፡ በአጭሩ ወግ-አጥባቂ ኢህአዴግዉያን ናቸዉ፤ ይህንን የሚሉ፡፡ ጊዜ  ደግነዉ ኢህአዴግን ከአብዮታዊነት ወደ ወግ-አጥባቂነት ዘለን አወረድነዉ፡፡ የወግ አጥባቂዎቹ  አባባል እዉነት እንኳን ቢሆን፤ ስልጣንን የግል እርስታቸዉ ያደረጉ ጥገኞችን አንጂ ኢህአዴግን እንደ ፖለቲካ ኃይል ሊያስደነግጠዉ  አይገባም፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ በራሱ  የመጨረሻ ዓላማዬ እራሴን አጥፍቼ  አዲስ ስርዓት መገንባት ነዉ ብሎ የሚያምን ድርጅት ነዉ፡፡ ይህ አዲስ ሰርዓት በገደበዉ የተያዘዉ  የአዉሮፓዉ ሶሺያል ዲሞክራሲም ሆነ ለቀቅ ያለዉ የአሜሪካዉ የሊብራል ዲሞክራሲ ዞሮ ዞሮ የኒዎ-ሊብራል ማዕቀፍ  ዉስጥ የሚወድቅ ነዉ፡፡ ግራም ቢሉ ቀኝ ዛሬ ከዚህ ዉጭ የለም፡፡ ለዚህ አዲስ ስርዓት እስካሁን ባየነዉ በኢትዮጵያ ዉስጥ መስራች አባት ለመሆን ጠቅላይ ሚኒሰትር ዓብይ አሕመድ የተሻሉ ሁነዉ ከተገኙ፤ ኢህአዴግ  ጸሎቴ ካሰብኩት ጊዜ በፊት  መልስ አገኘልኝ በማለት ከመደሰት ዉጭ የሚቆረቆርበት ምክንያት ግራ ያጋባል፡፡ በርግጥ ኢህአዴግ እራሱን ለየት አድርጎ ለማሳየት ልማታዊ መንግስት ነኝ ይላል፡፡ ይሄ እንኳን  ይነስም-ይብዛም ልማታዊ ያልሆነ መንግሰት በባሕሪ የሌለ በመሆኑ  ግፋ ቢሉት የማይገፋ ክርክር ነዉ፡፡ መችም የኒዎ- ሊብራል ቁንጮ የአሜሪካ መንግስት መሆኑ አያከራክርም ፤ እና የአሜሪካን መንግስት ነዉ ልማታዊ ያልሆነዉ! ዘመዶቻችን ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም የሚሉት እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥማቸዉ ነዉ፡፡ የኒዎ ሊብራል መንግስት ሆኖ ልማታዊ መሆን ይቻላል፤ የኮሚኒስት መንግስትም ሆኖ ልማታዊ መሆን ይቻላል፡፡ በሁለቱም መንገድ የልማቱ የመጨረሻ ግብ አትራፊ ይሁን አይሁን በርግጠኝነት ከወዲሁ ለመናገር የሚችል ሰዉ የለም፡፡ ያለጥርጥር ግን የሊብራሉ መንገድ ከኮሚኒስቱ በተሻለ ወደ አትራፊነት ማድረሱ ተፍትኖ የታየ ጉዳይ ነዉ፡፡ የኢህአዴግ መንግስትን  ልማታዊነቱን  ለጊዜዉ  እናቆየዉና ፤ ጠ/ሚኒስትር  ዓብይ አሕመድ  በቅርቡ ጭርሱኑ  ከጀርባዬ የኢኮኖሚ አሻጥር ደባ እየተደረገብኝ ነዉ ብለዋል፡፡ እኔ ለራሴ ግራ የገባኝ  አንድ ነጥብ አለ፡፡ የኢህአዴግ ሰዎች እንዲህ አገር  የወደደዉን  ዓብይ አህመድን ያመጣዉ የኛ የፖለቲካ መንገድ ነዉ፡፡ ድርጅታችን ሆደ-ሰፊ፤ ማንም ከታች ተነስቶ  ጣራ ላይ ሊያደረስ የሚያሰችል ብቁ  ምህዳር ያለዉ ስለመሆኑ ማረጋገጫዉ ይኽዉ ብለዉ የዓብይ አህመድን ዉጤታማነት ለምን የራሳቸዉም ማድርግ እንደተሣናቸዉ ባስበዉ ባስበዉ መልስ ብልጭም አላለልኝ፡፡ ያዉ እንግዲህ የተደበቀብኝ ነገር ቢኖር ነዉ እንጂ የተሣካለት ሰዉ ቡድን ዉስጥ  እንደ  አንዱ  አለመቆጠርን ማን ይፈልገዋል ተብሎ ይገመታል!
6- ሁለተኛዉ እንቅፋት የሚመጣዉ ከኢህአዴግ ዉጭ ያሉ የጠቅላይ ሚኒሰትር ዓብይ አሕመድ የፖሊቲካ ጠላቶች ሊባሉ ከሚችሉ ኃይሎች ነዉ፡፡ ዓቅማቸዉ አነስተኛ ቢሆንም ከዲሞከራሲም በላይ ዜጎች ናቸዉና ድምጻቸዉ ሊሰማ ግድ ይላል፡፡ ሆኖም ግን ፕራይቬታይዜሽን የሚባል ነገር አገር አጥፊ ነዉ አይሞከረም ማለት አንድ የፖሊቲካ አቋም  ነዉ፡፡ ወይንም ፕራይቬታይዜሽን ጥሩነዉ ሆኖም እነዚህ - እነዚህ  ነገሮች ይደረጉ ማለት ዓዋቂነት ነዉ፡፡ ድሮ ፕራይቬታይዜሽን ዛሬ ሲሉ ቆይተዉ፤ የጠቅላይ ሚኒሰትር ዓብይ መንግስት እሽ ልፈጽመዉ ነዉ ሲል በደምሳሳዉ መቃወም ግን እብድነት ሲጀምር  የሚታይ ምልክት ሣይሆን አይቀረም፡፡ እንደዚሁም፤ ከኤርትራ ጋር ስላም መፍጠር አለብን እያሉ፤ መልሶ አንዲት ቅንጣት መሬት አንሰጥም ሰዎቻችን ሞተዉበታል ማለት እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ሞቼ  እገኛለሁ ነዉ፡፡ በየጊዜዉ በምናየዉ እንደዚህ የሚሉ ሰዎች እነሱ የሞቱለት ጉዳይ ሣይሆን  በሞታቸዉ ላይ የተቃወሙት ነገር ይፈጸማል፡፡ 
7-   እንደገና ወደ ታሪክ እንመለስ፡፡ የሁለቱ መጠናቸዉ የሰማይና የመሬት ያህል ቢርቅም፤  ራስ ተፈሪም ሆኑ ኮሎኔል መንግሰቱ የገጠማቸዉን እንቅፋት ያስወገዱት በኃይል ነዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዓብይ ይህንን የማድርግ እድል ያላቸዉ አይመሰልም፡፡ ቢኖራቸዉም ለመጨረሻዉ አይጠቅማቸዉም፡፡ በሌላ በኩል እንደ ራስ ተፈሪም ሆነ እንደ ኮሎኔል መንግስቱ ሁሉ እሳቸዉም በሕዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ መቶ-ለመቶ ያሸነፈዉ ፓርላማ አባል ናቸዉ፡፡ ነገር ግን ይህ ፓርላማ ዛሬም ያለዉ  በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ እንዲሁም በለማ ቡድን አጠቃላይ የሕዝብ ተቀባይነት እና ተወዳጅነት እንጂ፤ እንደ ዓምና እና ካቻዓምናዉ የሕዝብ ተቃዉሞስ እስከሁን እራሱም ወደሚሄድበት  ሄዶ  ነበር!
8-  ይህንን ጎዶሎነት መሙላት የሚቻለዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጥታ የሕዝብ ዉሣኔ (ሬፈረንደም) ጥያቄን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማቅረብ የሥልጣናቸዉን ሕጋዊነት በማረጋገጥ ሥራቸዉን የተሣለጠ በማድረግ ነዉ፡፡ ይህ የዉሣኔ ሕዝብ ጥያቄዉ ፤ ጠ/ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ  ምን-ምን ተግባራትን መፈጸም እንደሚፈልጉ፤ ይህንን ለመፈጸም ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸዉ፤ እሳቸዉም ቢሆኑ ሰዉ ናቸዉ እና ስህተት እንዳይሰሩ የሚያያቸዉ ምን ዓይነት ተቆጣጣሪ ተቋም  እንደሚኖር፤ ትክክለኛዉን ምርጫ ለማድርግ ምን ያሕል ጊዜ እንደሚስፈልጋቸዉ በቀጥታ ለሕዝቡ በማቅረብ ይሁንታዉን በማግኘት የሚፈጸምባቸዉን ማናቸዉንም ደባ በተቻለ መጠን ከወዲሁ ማስወገድ ይቻላቸዋል፡፡ ይህ መንገድ በሕዝብ ምን ያህል ድጋፍ እንዳላቸዉ የሚያረጋግጥ ስለሚሆን፤  ያለጥርጥር  ከፖሊቲካ  ጠላቶቻቸዉ   ሽፋን  ይሰጣቸዋል፡፡  

OHHH.....IT IS D. TRUMP AGAIN

At long last, settlements have been reached in separate lawsuits between the Trump Organization and two celebrity chefs, Geoffrey Zakarian and José Andrés. The settlement between the organization and Andrés was agreed upon last Friday, while Zakarian’s was announced on Monday. Both lawsuits arose when the chefs “abandoned plans to set up shop in the Trump International Hotel, in Washington’s Old Post Office building” after President Trump kicked off is campaign back in 2015. As a result, the president sued both chefs.

ESTABLISHING A PRIVATE LIMITED COMPANY( P.L.C.) in ETHIOPIA

1. Prepare Memorandum of Association and Articles of Association.

The document can be prepared in Amharic and English but you might be asked to provide the Amharic version on District level. Take a closer look at the decision making part, specifically how much percentage is considered to be majority because when you change your address, increase your capital or any other major company decision, you will need to prepare a minutes that will be authenticated by Document Authentication & Registration Office. And unless the majority of the shareholders agree and present themselves in person at Document Authentication & Registration Office, your minutes will not be authenticated.
2. Check the company name.
You will take the draft Memorandum of Association and Article of Association to Ministry of Trade located next to Development bank of Ethiopia. There, they will check if there is any other company which resembles your company’s name and they will either tell you to change your company’s name or it will be accepted. If it’s accepted, they will give you permission to take memorandum of association and article of association to ministry of Document Authentication & Registration Office.

3. Authenticate your documents at Document Authentication & Registration Office.

Though there are many DARO office scattered around Addis Ababa, the only branch that deals with forming a company is the one located at Chelelek ALSAM Tower, around Ethiopian Commodity Exchange (ECX), located on the way from Mexico Square to Lideta / Tor Hayloch. After that, your documents will either be accepted and you and the share holders will be asked to present themselves in person or their legal representatives with a renewed ID Card or Passport. Now you have your PLC and you can now start the process to get a license.

የሥራ ውሎች፤ የሠራተኛ ሥራ እንዳይሠራ መከልከልና ለተወሰነ ጊዜ የማገልገል ወይም ካሣ የመክፈል ግዴታ፡፡


ሀ- እንደመግቢያ
በመጀመሪያ የሥራ ዉሎችን የሚገዙ ስንት ሕጎች  እንዳሉ መግለጽ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ሁለት ናቸዉ፡፡ እነሱም፡-
1-             በአዋጅ ቁጥር 377/1996 ሥር የሚተዳደሩ የሥራ ዉሎች፡፡ ይህ ሕግ በአሠሪና የሥራ አመራር (ማኔጅመንት) ኣባል ያልሆኑ ሠራተኞች ግንኙነታቸዉን የሚገዙበት ሕግ ነዉ፡፡ እዚህ ላይ ሁለት መሠረታዊ የሆኑ ነገር ግን ብዙ ጊዜ በአግባቡ ልብ የማይባሉ ነጥቦችን ጠቅሼ ልለፍ፡፡ አንደኛዉ  አሠሪዉና የሥራ አመራር (ማኔጅመንት) አባል የሆኑ ሠራተኞች ግንኙነታቸዉን በዚህ አዋጅ አማካኝነት  ለመግዛት ከፈለጉ  በስምምነታቸዉ መሰረት ይህንን ማድረግ ይችላሉ፡፡ በሥራዉ ዓለም ግን ይህ ሲደረግ አይታይም፡፡ ምክንያቱን የሚያዉቀዉ እግዛብሔር ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሁለተኛ፡፡ የሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 የአሠሪና ሠረተኛ ዋና ዋና ግዴታዎች ምን እንደሆኑ የሚዘረዝር ቢሆንም ፤ ሌሎች ተጨማሪ ግዴታዎች ግን በተጨማሪ ዉሎችም ሆነ በተጨማሪ ይዘቶች ተዋዋይ ወገኖች  እንዳይገቡ አይከለክልም፡፡
2-            በ1960 ዓ.ም. በወጣዉ የፍትሓብሔር ሕግ መሠረት የሚተዳደሩ የሥራ ዉሎች፡፡ ይህ ሕግ ተፈጻሚነቱ አሠሪና የሥራ መሪ (ማኔጅመንት) አባል  በሚገቡት የሥራ ዉል ላይ ነዉ፡፡ ከላይ እንደተመለከተዉ አሠሪና ሠራተኛዉ ይህ የፍትሓብሔር ሕግ ተፈጻሚ እንዳይሆንባቸዉና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት ግንኙነታቸዉ እንዲገዛ ለመምረጥ ይችላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለጸዉ የተለመደ አሰራር ግን አይደለም፡፡ ጠበቆች የደንበኞቻቸዉ መብት የበለጠ የሚጠበቅበትን ሁኔታ ቀድሞ በማየት ትክክለኛዉን አግባብ ሊያመላክቱ ይገባል፡፡
ለ- እያየን እንዳላየን...
ሌሎች  በጣም አስፈላጊ ሁነዉ እያለ የተዘነጉ ሁለት ዓበይት የሕግ ነጥቦችን ደግሞ ልጨምር፡፡ የመጀመሪያዉ ሠራተኛዉ ከአሠሪዉ ጋር ወደፊት እንዳይወዳደር ለማድረግ የፍትሓብሔር ሕጉ በግልጽ እዉቅና ሰጥቶና መሠረቶቹንም አስቀምጦ  እያለ አሰራሩ ግን ፍጹም ሊባል በሚችል ሁኔታ ጥቅም ላይ ሲዉል አይታም፡፡ በርግጥ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ይህንን መሰሉን ሁኔታ ሳይፈቅድም ሳይከለክልም ጉዳዩን በዝምታ አልፎታል፡፡ ሆነም ግን የአሠራሩን መፈቅድና መከልከል ለማወቅ  አንድ ነገር ብቻ ማየት ይበቃል፡፡ በሕግ መርህ መሠረት ያልተከለከለ ነገር ሁሉ የተፈቀደ  ነዉ፡፡ እዚህም ላይ ጠበቆች የደንበኞቻቸዉን ጥቅም በሚያራምድ መልኩ ሊመክሩ ይገባል፡፡  ሁለተኛዉ አንድን ሰዉ አሰልጥኖ በመቅጠር ለተወሰነ ጊዜ አሠሪዉን እንዲያገለግል የሚገደድበት የስምምነት ዉል አግባብ ነዉ፡፡ ይሄ በሁሉም ሕጎች በግልጽ ተደንግጎ እያለ የሚጠቀምበት ሰዉ ግን ያለም አይመስልም፡፡ ምክንያቱ አለማወቅ ይሁን  አለመፈለግ አሁንም  ግልጽ አይደለም፡፡ ምንአልባት ጥያቄዉ በራሱ መልሱን ይናገራል ካልተባለ በቀር፤ አንድ ነጥብ ላንሣ፡፡ ለመሆኑ አንድ አሠሪ ሠራተኘዉ ወደፊት በጥራትና በብቃት እንደሚያገለግለዉ እርግጠኛ ካልሆነ በቀር ምን ቢሆነኝ ብሎ  በራሱ ኪሣራ "ብቁ" ያልሆነን ሠራተኛ ቀጥሮ ያሰራዋል? ለምንስ ብሎ ያሰለጥነዋል? የዚህ ጥያቄ ትክክለኛ  መልስ  የአሰራሩ ሕጋዊነትና ሕገወጥነት የሚወድቀዉ በአሰሪዉና ሠራተኛዉ ስምምነት አረቃቀቅ እንጂ በሕጎቹ ክልከላ ላይ ስላለመሆኑ ግልጽ ያደርገዋል፡፡  
ሐ - የታተሙ የሠበር ችሎት ዉሣኔዎች በሠራተኛ ትምሕርትና ሥልጠና ጉዳዮች ላይ፡፡
ደግነቱ የሠበር ችሎት ተመሣሣይ በሆኑ ጉዳዮች ከላይ የተመለከቱት ግንዛቤዎች ሕጋዊ ስለመሆናቸዉ ተደጋጋሚ አስገዳጅ ዉሣኔዎችን ሰቷል፡፡ ለዓብነት ያሕል እነዚህ የታተሙትን ከዚህ በታች ገልጫለሁ፡፡
1-   በአመልካች / ሃርሴማ ሰለሞን እና መልስ ሰጪ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (የ//. 33473፤ ቅጽ 8)፤ ገጽ 322፡፡
2-   በአመልካች የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንቲትዩት እና ተጠሪ አቶ ተፈሪ ማሞ (የ// 49453፤ ቅጽ 9)፤ ገጽ 192፡፡
3-  (አመልካች ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ተጠሪዎች እነ ዮናስ ካሳ (ሁለት ሰዎች)፤ (የሠ// 46574፤ ቅጽ 12)፤ ገጽ 90፡፡